የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኮዬ ፈጬ የጋራ መኖሪያ ቤት ነዋሪዎችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው ተብሏል

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኮዬ ፈጬ የጋራ መኖሪያ ቤት ነዋሪዎችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት ኮዬ ፈጬ ቁጥር 1 እና 2 የጋራ መኖሪያ ቤት ሳይቶች ላይ ጊዜያዊ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታና በየብሎኩ ባለሶስተ ፌዝ ቆጣሪ የገጠማ ስራ በመከናወን ላይ እንደሚገኘ ተገልጿል፡፡ በዚህም በኮዬ ፈጬ ቁጥር 1 ሳይት የመስመር ዝርጋታና የ13 ትራንስፎርመሮች የተከላ ስራ ተከናውኗል፤ በ126 ብሎኮች ላይ ቆጣሪዎች እንዲገጠሙ የተደረገ ሲሆን ለቀሪ 147 ብሎኮች ቆጣሪዎችን ለመግጠም ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ተነግሯል፡፡ በተመሳሳይ በኮዬ ፈጬ ቁጥር 2 ሳይት ካሉ 788 ብሎኮች ውስጥ ከፓርሴል 1 እስከ 64 ለተካተቱ ብሎኮች አገልግሎት የሚሰጥ የመስመር ግንባታ መጠናቀቁ ተመላክቷል፡፡ 21 ትራንስፎርመሮች እንዲተከሉ የተደረገ ሲሆን ከፓርሴል 65 እስከ 76 ስር ላሉ ብሎኮች ደግም የመስመር ዝርጋታ ስራ እየተሰራ ይገኛልም ተብሏል፡፡ መደበኛው ግንባታው ሲጠናቀቅ በሁለቱም ሳይቶች ከ60 ሺ በላይ ነዋሪዎችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ከአገልግሎቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

It is said that the Ethiopian Electricity Service is working to provide electricity service to the residents of the Koye Feche condominium. Currently, it is stated that the construction of temporary electricity lines and the installation of three-phase meters in each block is being carried out on the sites of Koye Fete No. 1 and 2 condominiums. In this way, the line laying and the installation of 13 transformers were done at Koye Fetke No. 1 site; It is said that meters have been installed in 126 blocks and work is underway to install meters in the remaining 147 blocks. In the same way, it was noted that the construction of a line that will serve the blocks included from Parcel 1 to 64 out of 788 blocks in Koye Fetke No. 2 site has been completed. It is said that 21 transformers have been installed and line laying work is being done for the blocks under Parcel 65 to 76. The information we received from the service indicates that when the normal construction is completed, more than 60,000 residents will benefit from electricity at both sites.

Leave a Reply