የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በሸገር ደርቢ ጨዋታ ጅማሮውን ያደርጋል

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቻን ውድድር ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የሀገራችን ከፍተኛው የሊግ እርከን ውድድር የፊታችን ቅዳሜ እንደሚጀመር የውድድሩ የበላይ አካል ይፋ አድርጓል። ጨዋታዎቹ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ሲደረጉ በመክፈቻ ቀን መርሐ-ግብርም ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉት ተስተካካይ ጨዋታ እንደሚደረግ ተመላክቷል። በማግስቱ እሁድ ደግሞ ሌላኛው የወላይታ ድቻ እና ሲዳማ ቡና ተስተካካይ ጨዋታ ይደረጋል። መደበኛ የ14ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በበኩላቸው በቀጣዩ ሳምንት ሀሙስ ጥር 25 ጅማሮዋቸውን ያደርጋሉ።

 

The governing body of the competition has announced that the highest league level competition of our country, which was interrupted due to the Chan competition of the Ethiopian national team, will start next Saturday. When the games will be held at Adama Science and Technology University, it has been indicated that a match between Saint George and Ethiopia Coffee will be played on the opening day schedule. On the following Sunday, another match will be played between Wolaita Dacha and Sidama Buna. Regular Week 14 games will begin next week on Thursday, January 25.

Leave a Reply