” ኮርፖሬሽኑን ለእዳ የዳረጉ የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች የሕግ እርምጃ ይወሰድባቸው ” – የሕ/ተ/ም/ቤት

” ኮርፖሬሽኑን ለእዳ የዳረጉ የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች የሕግ እርምጃ ይወሰድባቸው ” – የሕ/ተ/ም/ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ..የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ፤ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን በቀጣዮቹ 3 ወራት የአዳማ_አዋሽ መንገድ ጥገና የውል ስምምነት ላይ አስቸኳይ እልባት እንዲሰጥ አሳሰበ። ቋሚ ኮሚቴው ” ያልተገባ ውል ባለው ” ስምምነት ኮርፖሬሽኑን ለእዳ የዳረጉ የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች የሕግ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ጠይቋል።ቋሚ ኮሚቴው ይህ የጠየቀው የኮርፖሬሽኑን የ2013 እና 2014 ዓ.ም የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት ላይ በተወያየበት ወቅት ነው። ኮርፖሬሽኑ ከደንበኞች በውል የተረከባቸውን ፕሮጀክቶች ውል በተገባበት ጊዜ ገደብ የማይፈጸሙ መሆናቸው ተመላክቷል። በአዋጅ ወደ ሌሎች የመንግስት ተቋማት እንዲተላለፉ የተወሰኑ ሃብቶች ግምትና ዕዳ ያልተገመተና በውሳኔው መሰረት ርክክብ እንዳልተደረገ ተገልጿል። ኮርፖሬሽኑ ኮንትራት ወስዶ ለሰራቸው ስራዎቹ በአጠቃላይ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ አለመሰብሰቡም ተጠቁሟል። በኮርፖሬሽኑ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ ግንባታቸው የሚጠናቀቅ መሆኑ ቢቀመጥም ፕሮጀክቶች በታቀደላቸው መሰረት ያልተከናወኑ ናቸው ተብሏል። ከግንቦት 24 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ የአዳማ አዋሽ መንገድ ጥገና እና መንገዱን ለማስተዳደር ስምምነት ገብቶ እየሰራ ቢሆንም በውሉ መሰረት ሥራውን ባለማከናወኑ ለበርካታ ዕዳ መጋለጡ ነው የተነገረው። ከዚህም አልፎ ኮርፖሬሽኑ ከ14 ሚሊየን ብር በላይ ከአሰሪ ተቋም ክፍያ መሰብሰብ አልቻለም ተብሏል።

 

“Legal action should be taken against the officials and professionals who have caused the corporation debt” – Standing Committee on Public Expenditure Management and Control of the University. House of Representatives Standing Committee on Government Expenditure Management and Control; He urged the Ethiopian Construction Works Corporation to urgently settle the contract for the maintenance of #Adama_Awash Road within the next 3 months. The Standing Committee demanded that legal action should be taken against the officers and professionals who have made the corporation indebted with the “unfair contract” agreement. The Standing Committee made this request while discussing the 2013 and 2014 operational audit report of the corporation. It has been pointed out that the projects that the corporation has contracted from customers are not fulfilled at the time of signing the contract. It has been stated that certain assets and debts were not estimated and handed over according to the decision to be transferred to other government institutions by decree. It was also pointed out that the corporation did not collect more than 1 billion birr for the works it contracted. It is said that the construction of the corporation’s projects will be completed on time, but the projects have not been completed as planned. From May 24, 2008 Since then, he has entered into an agreement to maintain and manage the Adama Awash road, but it is said that he has been exposed to several debts due to not carrying out the work according to the contract. Furthermore, it is said that the corporation could not collect more than 14 million birr from the employer.

 

 

 

Leave a Reply