ማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋች ለማስፈረም ተቃርቧል !
የመሀል ሜዳ ተጨዋቻቸው ክርስቲያን ኤሪክሰን በጉዳት ምክንያት ለወራት ያጡት ማንችስተር ዩናይትዶች አዲስ አማካይ በውሰት ለማስፈረም ተቃርበዋል።
በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የሚመሩት ማንችስተር ዩናይትዶች የባየር ሙኒኩን የመሀል ሜዳ ተጨዋች ማርሴል ሳቢትዘር በውሰት እስከ ውድድር አመቱ መጨረሻ ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል።
የባየርሙኒክ ቦርድ ተጨዋቹ በውሰት ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ለሚያደርገው ዝውውር ፍቃድ መስጠታቸው ተገልጿል።
ኦስትራያዊው የ 28ዓመት ተጫዋች ማርሴል ሳቢትዘር ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ለሚያደርገውን ዝውውር የህክምና ምርመራውን ለማድረግ ምሽት ወደ እንግሊዝ እንደሚያመራ ተዘግቧል።
Manchester United, who lost their midfielder Christian Eriksen for months due to injury, are close to signing a new midfielder on loan.
Manchester United, led by coach Erik Tenhag, are on the verge of signing Bayern Munich midfielder Marcel Sabitzer on loan until the end of the season.
It is stated that Bayern Munich’s board has given permission for the player’s loan transfer to Manchester United.
It is reported that the 28-year-old Austrian player Marcel Sabitzer will go to England in the evening to undergo a medical examination for his transfer to Manchester United.