La Liga’s semi-annual Best African Player award competition is set for the second time. It is stated that it is possible to vote on this competition, which is organized to commemorate the great contribution of the African continent to the Spanish La Liga, from January 8-21/2015. The election is open to the public on LaLiga’s social media pages in Africa and around the world, and it is also a platform for journalists in Africa to vote, including ourcountry.
LaLiga has also announced that it has prepared various exciting prizes for fans who vote in the voting process.
የላሊጋ የግማሽ ዓመት ምርጥ አፍሪካዊ ተጨዋች ሽልማት ውድድር ለሁለተኛ ጊዜ ተዘጋጀ። የአፍሪካ አህጉር ለስፔን ላሊጋ ያበረከተውን ትልቅ አስተዋጽኦ ለመዘከር በሚዘጋጀው በዚህ ውድድር ላይ ከጥር 8-21/2015 ዓ.ም ድምፅ መስጠት እንደሚቻል ተገልጿል። ምርጫው በላሊጋ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ በአፍሪካ እና በመላው አለም ለህዝብ ክፍት ሲሆን ሀገራችንን ጨምሮ በአፍሪካ የሚገኙ ጋዜጠኞችም ድምፅ የሚሰጥቡት መድረክ ነው።
ላሊጋ በምርጫው ሒደት ላይ ድምፅ ለሚሰጡ ደጋፊዎች የተለያዩ አስደሳች ሽልማቶችን ማዘጋጀቱንም ገልጿል።