Manchester City defender Joao Cancelo is close to joining German club Bayern Munich on a loan deal. Portuguese player Joao Cancelo has arrived in Munich to undergo a medical examination for his transfer to Bayern Munich, and the transfer is expected to be announced in the next few hours. The 28-year-old player Joao Cancelo will join Bayern Munich on loan, and it is stated that the contract includes an option to sign permanently for Bayern Munich for 70 million euros.
የማንቸስተር ሲቲው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ጇ ካንሴሎ በውሰት ውል የጀርመኑን ክለብ ባየር ሙኒክ ለመቀላቀል ተቃርቧል። ፖርቹጋላዊው ተጨዋች ጇ ካንሴሎ ወደ ባየር ሙኒክ ለሚያደርገውን ዝውውር የህክምና ምርመራውን ለማድረግ ሙኒክ የደረሰ ሲሆን በቀጣይ ሰዓታት ዝውውሩ ይፋ እንደሚደረግ ይጠበቃል። የ 28ዓመቱ ተጫዋች ጇ ካንሴሎ ባየር ሙኒክን በውሰት የሚቀላቀል ሲሆን በኮንትራት ውስጥ ለባየር ሙኒክ በ70 ሚልዮን ዩሮ በቋሚነት የማስፈረም አማራጭ እንደተካተተበት ተገልጿል።