አሁን ላይ በተገኘው አንፃራዊ ሰላም የኮንቮይ ጉዞ ያለምንም ችግር #በአንድ_ቀን መድረስ ችሏል ” – ኢ/ር በላቸው ካሳ የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እየተካሄደ በሚገኝበት ቀጠና በተገኘው ሰላም የግድቡ ግንባታ እየተፋጠነ መሆኑ ተገልጿል። የግድቡ ምክትል ስራ አስኪያጅ የሆኑት ኢንጂነር በላቸው ካሳ ፤ ” በቀጠናው የተገኘው አስተማማኝ ሰላም የግድቡን የግንባታ ሂደት #እያፋጠነው ይገኛል ” ሲሉ አሳውቀዋል።” የፀጥታው ጉዳይ ለግድቡ ግንባታ መሠረታዊ ፍላጎት መሆኑን በመገንዘብ #የሀገር_መከላከያ_ሰራዊት ከሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ጋር ተቀናጅቶ ተልዕኮውን በጀግንነት በመፈፀም በቀጠናው የከፈለው መስዋዕትነት የኢትዮጵያን ህዝብና መንግስት ያኮራ በታሪክ የሚኖር ነው ” ብለዋል። ኢ/ር በላቸው፤ በቀጠናው በነበረው የሰላም ችግር ምክንያት ወደ ግድቡ የሚመላለሱ ተሽከርካሪዎች ከሁለትና ከሶስት ቀን በላይ በመቆም መስተጓጎል ይፈጥር እንደነበር አስታውሰው አሁን ላይ የኮንቮይ ጉዞ በተገኘው አንፃራዊ ሰላም ያለምንም ችግር #በአንድ_ቀን መድረስ መቻሉን አስረድተዋል። የግድቡን ግንባታ ዳር ለማድረስ ሌት ተቀን ሃያ አራት ሰዓት ያለ ዕረፍት የሚተጉ የግንባታዉ ሰራተኞች የአካባቢውን የሙቀት ሁኔታ ተቋቁመው ታሪካዊ ሃላፊነታቸውን በደማቅ ሞራል እየተወጡ እንደሚገኙ አረጋግጠዋል። በስፍራው ከሚገኙ የሀገር መከላከያ አባላት የቀጠናውን ዘላቂ ሰላም በአስተማማኝ የዝግጁነት ደረጃ በማረጋገጥ ሰራዊቱ የተሰጠውን ግዳጅ በሞራል እየተወጣ እነደሆነ ተናግረዋል።ሰራዊቱ የሀገሪቱን ሰላም የማይፈልጉ ፀረሠላም የሆኑ ኃይሎችን ፍላጎት በማምከን የግድቡን የፍፃሜ ትንሳኤ ለማብሰር ደከመኝ ሳይል ሀገራዊ ተልዕኮዉን እየተወጣ ነው ብለዋል።
“With the relative peace that has been achieved now, the convoy journey was able to reach in one day without any problems” – Er. It is stated that the construction of the dam is speeding up due to the peace found in the area where the construction of the Ethiopian Great Renaissance Dam is underway. Engineer Belet Kasa, who is the deputy manager of the dam; “The safe peace found in the area is speeding up the construction process of the dam,” they announced. Recognizing that the security issue is a fundamental need for the construction of the dam, the #national_defence_army” combined with other security forces and carried out its mission bravely, the sacrifices made in the region will make the people and government of Ethiopia proud and live in history,” he said. Say to Mr. He recalled that due to the peace problem in the region, the vehicles going to the dam used to stop for more than two or three days and cause disruption. The construction workers, who are working twenty-four hours a day to complete the construction of the dam, have confirmed that they are carrying out their historical responsibility with a strong morale, withstanding the heat conditions of the area. The members of the national defense at the place said that the army is morally fulfilling its duty by ensuring the permanent peace of the region with a safe level of readiness. He said that the army is carrying out its national mission tirelessly to announce the final resurrection of the dam by sterilizing the needs of the anti-peace forces who do not want the peace of the country.