በለሚ ኩራ ክ/ከተማ በትናንትናው እለት ምሽት 4፡48 ላይ ከፍተኛ ቴክኖሎጂና ግብዓት የፈሰሰበት የክ/ከተማው አስተዳደር ህንፃ የእሳት አደጋ ደርሶበት ውድመት ደርሷል። የአደጋው ምክንያት እና መንስኤ በፖሊስ ምርመራ እየተካሄደበት ሲሆን ምርመራው እንዳለቀ ለህዝብ ይፋ ይደረጋል ተብሏል። የአካባቢው ማህበረሰብ ከአደጋው ጋር ተያይዞ ማንኛውንም መረጃዎች በመስጠት የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል። ትላንት ውድመት የደረሰበት ህንፃ የኢትዮ ቴሌኮም ፤ የአርቴፊሻል ኢንተልጀንስ ፤ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ተቋማት የተሳተፉበት እና የዲጂታል አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ህንፃ የነበረ ሲሆን ቅዳሜ ለምረቃ እንዲበቃ ሲሰራ ነበር ተብሏል።
At 4:48 pm yesterday in Lemi Kura sub-city, the administrative building of the city where high technology and resources were poured was destroyed by fire. The reason and cause of the accident is being investigated by the police and will be made public once the investigation is complete. The local community is called upon to cooperate with the disaster by providing any information. Ethio Telecom’s building that was destroyed yesterday; Artificial Intelligence; It is said that there was a building where information network security institutions were involved and it was possible to provide digital services, and it was said to be ready for graduation on Saturday.