” በብሔራዊ ፈተናው ከ600 በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን የዩኒቨርሲቲ ወጪ እንሸፍናለን ” – አማራ ባንክ በ2014 ዓም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው በመላ ሀገሪቱ ከ600 በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን የዩኒቨርሲቲ ወጪ እንደሚሸፍን አማራ ባንክ አሳውቋል። ባንኩ በመላው ሀገሪቱ ከ600 በላይ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው በወር 750 ብር እየከፈለ እንደሚያስተምር የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሄኖክ ከበደ ገልጸዋል። ይህ ውሳኔ የባንኩ የማኀበረሰባዊ አገልግሎት አካል መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ለአሚኮ ጠቁመዋል። በመላ ሀገሪቱ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር እውቅናና ሽልማት ይሰጣቸዋል መባሉ ይታወሳል።
“We will cover the university expenses of students who scored more than 600 in the national exam” – Amara Bank . Amhara Bank has announced that it will cover the university expenses of students who took the 12th class exit exam and scored more than 600 results in the 2014 school year. The bank’s chief executive, Henoch Kebede, said that the bank is paying 750 birr per month to each of the 600 students who have achieved good results. The CEO pointed out to Amico that this decision is part of the bank’s social service. It is said that students who achieve high results across the country will be recognized and awarded by the Ministry of Education.